ሰላም እንዲመጣ መንግሥት ምን አደረገ ?
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
“ዛሬ በምስራቅ ሸዋ ዞን የነበረን ጉብኝት በክረምት የስንዴ ምርት ሥራዎች የተገኘውን ውጤት የምርት አሰባሰቡን በመመልከት ለመገምገም እና የበጋ ስንዴ ሥራ ማስጀመር ላይ ያተኮረ ነበር። በዚያው አካባቢ የሙዝ፣ ፓፓያ እና አሳ ክለስተር ሥራዎችንም ተመልክተናል። ነባሩ ባሕላዊ የግብርና ዘዴ አሁንም ያለ ቢሆንም በሰፊው ለማረስ የሚያስችለው ሜካናይዜሽን እያደገ በመሄዱ የአካባቢውን የግብርና ብቁነት እና ምርታማነት እያሳደገ ይገኛል። ወደኋላ መለስ…
“ኢትዮጵያ ውስጥ የሚያስፈልገው ብቸኛው መንገድ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ነው፡፡ ችግሮች አሉኝ የሚሉ አካላት ጋር ቁጭ ብሎ በመነጋገር ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት አሁንም በራችን ክፍት ነው። የኢትዮጵያን እድገት የማይሹ ሀገራት በጦርነት እንደማያሸንፉን ያውቁታል፡፡ ያላቸው ምርጫ ባንዳዎችን መላክ ነው። ኢትዮጵያን በቅጡ ያላወቁ የውስጥ ባንዳዎች ደግሞ ከጠላት ጋር በማበር ዓላማቸውን የሚያሳኩ ይመስላቸዋል፡፡ ይህ ፈጽሞ ሊሳካ አይችልም። “ ጠቅላይ…
ባሳለፈነው በጀት ዓመት የግብርና ዘርፍ 7 ነጥብ 3 በመቶ ዕድገት ያሰመዘገበ ሲሆን ከአጠቃላይ ዕድገታችን ዉስጥ ግብርና 2 ነጥብ 3 ድርሻ አለዉ፡፡ ከግብርና ምርት አንጻር ከሪፎርሙ በፊት በ2010 ዓ.ም የኢትዮጵያ የሩዝ ምርት 1.5 ሚሊዮን ኩንታል ሲሆን ባለፈዉ ዓመት ግን 63 ሚሊዮን ኩንታል ሩዝ ማምረት ተችሏል። ይህ የሩዝ ምርት በኢኮኖሚዉ እድገት ዉስጥ ትልቅ ለዉጥ መኖሩን የሚያሳይ ነዉ፡፡…
ባለፉት 6 አመታት ሕዝብን በማስተባበር በተሰራው የአርንጓዴ ዐሻራ መረሃ ግብር 25 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ተሳትፈው 48 ቢሊዮን ችግኞችን ተክለዋል፡፡ አንድ ችግኝ ከመጀመሪያው ዝግጅት ጀምሮ እስከመጨረሻ ድረስ 1 ዶላር ወጪ ቢፈጅ እንኳን ኢትዮጵያዊያን ለሀገራቸው 48 ቢሊዮን ዶላር ገዳማ ኢንቨስት አድርገዋል እንደማለት ነው ፡፡ ይህን ያህል ገንዘብ የሚያበድረን ሃገርም ሆነ የሚለግሰን ተቋም የለም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶር)…
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሕዝብ ተወካዎች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሳባ ላይ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በኢኮኖሚው ዘርፍ ለተነሱላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ ኢትዮጵያ የብዝሃ የኢኮኖሚ ፖሊሲ በመከተሏ ዘርፈ ብዙ ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከዚህ ቀደም ግብርና መር የነበረው፣ አሁን ግብርናን ጨምሮ በማኑፋክቸሪንግ ፣በማዕድን፣ በቱሪዝም ፣በእንዱስትሪ እና በተክኖሎጂ…
የኢትዮጵያን አቅም ላኪው ያውቀዋል ተላላኪው ግን ይጓጓል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያን ዕድገት የማይፈልጉ ሀገራት በጦርነት ሊያሸንፉን እንደማይችሉ ያውቁታል። ነገር ግን የኢትዮጵያን አቅም ላኪው ቢያውቀውም ተላላኪው ግን ይጓጓል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡ ኢትዮጵያ ደካማ ሆና እንድትኖር ኢትዮጵያ በሁለት እግሯ መቆም እንዳትችል የሚሹና የሚሰሩ ሀገራት ባሉበት ሁኔታ ኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅምን ለይተው…