የሕፃናት ቅድመ መደበኛ ትምህርት ለኢትዮጵያ ቁልፍ በዘርፉ የተወሰደ የማስተካከያ እርምጃ ነው።
ምክንያቱም ህፃናት በትምህርታቸውና በህይወታቸው ስኬታማ እንዲሆኑ የሚያስፈልጋቸውን ክህሎትና እውቀት በማስጨበጥ ለዘላቂ ትምህርትና ለግል ስኬታማነት መሰረት ይጥላል። ጥራት ያለው የቅድመ-መደበኛ ትምህርት ተደራሽነትን ለማስፋፋት፣ መምህራንን ለማሰልጠን፣ ደህንነቱ የተጠበቀና ምቹ የመማሪያ አካባቢን ለመፍጠር በሀገር አቀፍ ደረጃ በሺዎች የሚቆጠሩ የመዋለ ህፃናት ትምህርት ቤቶች እየተቋቋሙ ይገኛሉ። ቅድመ መደበኛ ትምህርት አገልግሎት ባልተዳረሰባቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ዘንድ በመድረስ እኩልነትን ያረጋግጣል፣ ማህበራዊና የአስተሳሰብ እድገትን…

