የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ አመለካከት የመቅረጽ እና ብሔራዊ ጥቅሞችን የማስገንዘብ ሚናዉን በላቀ ደረጃ እንዲወጣ መንግሥት አሳሰበ።
“ዓላማ ተኮር ተግባቦት ለሀገር ግንባታ” በሚል መሪ መልእክት የፌዴራል ተቋማት የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን የሥራ ኃላፊዎችና ከፍተኛ ባለሙያዎች ውይይት ተካሂዷል፡፡ በአፍሪካ የአመራር ልሕቀት አካዳሚ ዛሬ የተካሄደዉ የውይይት መድረክ ላይ የዘርፉን አጠቃላይ አቅጣጫ ያመላከቱት የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሠ ቱሉ (ዶ.ር) ባለፉት ጥቂት የለውጥ ዓመታት በተመዘገቡ ኹለንተናዊ ስኬቶች የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ ጉልህ ሚና መጫወቱን አውስተዋል፡፡ ኢትዮጵያ በተፈጥሮ…
