የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት
የጽናት ቀን “ኢትዮጵያን ስናስብ፣ ሌት ተቀን በጽናት በመቆም ሀገርን ከጠላት ለመጠበቅ ወጥተው ለሚያድሩት ብርቱ የፀጥታ ኃይሎቻችን ቅድሚያ ሳንሰጥ ስለ ሁለንተናዊ ከፍታ ማሰብ ፈጽሞ አይቻልም፡፡ ለዚህም ነው በዚህ የጽናት ቀን፣ ለሀገረ-መንግሥታችን ዘላቂነትና ሉዓላዊነት ሲሉ ውድ ሕይወታቸውን የከፈሉትን የጀግኖቻችንን ታሪካዊ መስዋዕትነት በከፍተኛ ሀገራዊ ክብር የምንዘክረው፡፡ ዛሬ ላይ ሀገራችን በራሷ ዕውቀትና በልጆቿ አቅም የላቀ የቴክኖሎጂ ብቃት ያላቸውን ሰው…
